Skip to main content

Posts

Showing posts from May, 2026
  የታሰበው ሰላማዊ ሰልፍ መተላለፉን ለማሳዎቅ ከሰላማዊ ሕዝባዊ እምቢተኝነት ትግል ድጋፍ ሰጪዎች የጋራ-መድረክ (የጋራ-መድረክ) የተሰጠ መግለጫ   በኢትዮዽያ ውስጥ ያለውን ጨቋኝ አምባ ገነን አገዛዝ ለማስወገድ     ጠንካራና አንድ ወጥ ሰላማዊ የህዝባዊ እምቢተኝነት ትግል መካሄድ አለበት ብለን የምናምንና በውስጣችን ከ 50 በላይ ንዑሳን ስብስቦችን አካተን የምንገኝ ዘጠኝ ድርጅቶች ከአንድ ወር በፊት የጋራ - መድረክ የመሰረትን መሆኑ ይታዎቃል። የጋራ - መድረካችን ህዝባችን ወደ ውጤታማ የህዝባዊ እምቢተኛነት ትግል መሸጋገር ይችል ዘንድ በቅድሚያ ተቃዋሚ ኃይሎች በጋራ የህልውናችን አጀንዳ ዙሪያ ተሰባስበን አገዛዙን በትብብር መታገል አለብን የሚል ዓላማ ይዘን ያቋቋምነው መድረክ ነው። ይህንን ዓላማ እውን ለማድረግ የሚያስችሉ ፈርጀ ብዙ ጥረቶችን በአሁኑ ወቅት እያደረግን እንገኛለን። ከእነዚህ ጥረቶቻችን ውስጥ አንዱ በዋሽንግተን ዲሲ እና በለንደን ከተሞች ሁሉም ተቃዋሚ የፖለቲካ ኃይሎች፣ ሲቪክ ማህበራትና መገናኛ ብዙሃን በጋራ ተባብረው የሚያዘጋጇቸው፤ ህዝቡ የብሄር፣ የኃይማኖትና የፖለቲካ ርዕዮት ዓለም ልዩነቶችን በተሻገረ አግባብ እጅ - ለእጅ ተያይዞ በነቂስ በመውጣት የሚታደምባቸው፣ ሰላማዊ ሰልፎችን ሚያዝያ 23 ቀን 2018 ዓ . ም ለማካሄድ አቅድ ይዘን እየተንቀሳቀስን መሆኑን ከወራት በፊት አሳውቀን እንደነበር ይታዎሳል።   ነገር ግን በውጭ አገር የሚገኙ ኢትዮ ጵ ያውያን     ካለፈው ሳምንት ጀምሮ እስከ ሚያዚያ ...