የታሰበው ሰላማዊ ሰልፍ መተላለፉን ለማሳዎቅ ከሰላማዊ ሕዝባዊ እምቢተኝነት
ትግል ድጋፍ ሰጪዎች የጋራ-መድረክ (የጋራ-መድረክ) የተሰጠ መግለጫ
በኢትዮዽያ ውስጥ ያለውን ጨቋኝ አምባ ገነን አገዛዝ ለማስወገድ ጠንካራና አንድ ወጥ ሰላማዊ የህዝባዊ እምቢተኝነት ትግል መካሄድ አለበት ብለን የምናምንና በውስጣችን ከ50 በላይ ንዑሳን ስብስቦችን
አካተን የምንገኝ ዘጠኝ ድርጅቶች ከአንድ ወር በፊት የጋራ-መድረክ የመሰረትን መሆኑ ይታዎቃል። የጋራ-መድረካችን
ህዝባችን ወደ ውጤታማ የህዝባዊ እምቢተኛነት ትግል
መሸጋገር ይችል ዘንድ በቅድሚያ ተቃዋሚ ኃይሎች በጋራ
የህልውናችን አጀንዳ ዙሪያ ተሰባስበን አገዛዙን በትብብር
መታገል አለብን የሚል ዓላማ ይዘን ያቋቋምነው መድረክ ነው። ይህንን ዓላማ እውን ለማድረግ የሚያስችሉ ፈርጀ ብዙ
ጥረቶችን በአሁኑ ወቅት እያደረግን እንገኛለን። ከእነዚህ
ጥረቶቻችን ውስጥ አንዱ በዋሽንግተን ዲሲ እና በለንደን ከተሞች ሁሉም ተቃዋሚ የፖለቲካ ኃይሎች፣ ሲቪክ ማህበራትና መገናኛ ብዙሃን በጋራ ተባብረው የሚያዘጋጇቸው፤ ህዝቡ የብሄር፣ የኃይማኖትና የፖለቲካ ርዕዮት ዓለም ልዩነቶችን በተሻገረ አግባብ እጅ-ለእጅ ተያይዞ በነቂስ
በመውጣት የሚታደምባቸው፣ ሰላማዊ ሰልፎችን ሚያዝያ 23 ቀን 2018 ዓ.ም ለማካሄድ አቅድ ይዘን እየተንቀሳቀስን መሆኑን ከወራት በፊት
አሳውቀን እንደነበር ይታዎሳል።
ነገር ግን በውጭ አገር የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ካለፈው ሳምንት ጀምሮ እስከ ሚያዚያ 23 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ በተለያዩ
የዓለም አገራት አገዛዙ በኢትዮጵይ ህዝብ ላይ እየፈጸመ
የሚገኘውን ሁለንተናዊ ወንጀል በመቃዎም ተከታታይ
ሰልፎችን እያካሄዱ መሆኑን ግንዛቤ ውስጥ በማስገባት፣ የሰላማዊ ሰልፎቹን ተደራራቢነት
ለማስቀረት እኛ አስበነው የነበረውን ሁሉን አቀፍ ሰላማዊ ሰልፍ ላልተወሰነ ጊዜ እንዲራዘም የወሰንን መሆኑን ለማሳወቅ እንወዳለን።
በውጭ አገር የሚገኙ ኢትዮዽያውያን እያካሄዷቸው የሚገኙትን ሰላማዊ ሰልፎች
ዓላማም ሁላችንም የምንጋራው በመሆኑ ሁሉም የህብረተሰብ
ክፍል ለሰልፎቹ ስኬታማነት አጋርነቱን እንዲያሳይ በዚህ
አጋጣሚ ጥሪያችንን እናቀርባለን።
ጦርነት ይቁም! ሰላም ይስፈን! የግፍ አገዛዝ ያብቃ! ከምርጫ በፊት ሽግግር ይኑር!!
ስንተባበር እናሸንፋለን!!
ግንቦት 1 ቀን 2018 ዓ.ም
Comments
Post a Comment